Magazine

ራሴን አጠፋሁ- በኤፍሬም እንዳለ ወደ አማርኛ ተመልሶ ለገበያ ቀረበ

ራሴን አጠፋሁ- በኤፍሬም እንዳለ ወደ አማርኛ ተመልሶ ለገበያ ቀረበ

የእውቁ ቱርካዊ ደራሲ አዚዝ ኔሲን የአጫጭር ልብ ወለዶች መድብል “ራሴን አጠፋሁ” በሚል ርዕስ በአዲስ አድማሱ አምደኛ በኤፍሬም እንዳለ ወደ አማርኛ ተመልሶ ለገበያ ቀረበ፡፡

አዚዝ ኔሲን ቱርክ ካፈራቻቸው ደራስያን ከግንባር ቀደሞቹ አንዱ ሲሆን በስራዎቹ በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ ስራዎቹም በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል፡፡
አዚዝ ኔሲን ልዩ ከሚያደርጉት ባህርያት ዋናው የሚያነሳቸው ማህበራዊና ፖለቲካዊ ርዕሶች ጥንካሬ ነው፡፡ “ራሴን አጠፋሁ” ውስጥ የተካተቱት አጫጭር ልብ ወለዶችም ይህንኑ ያንጸባርቃሉ፡፡ በዚህም አቋሙ ደራሲው በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት ተዳርጓል፡፡ ከረዣዥም ልብ ወለዶቹና ሌሎች የስነ ጽሁፍ ስራዎች በተጨማሪ ወደ ሁለት ሺ ገደማ አጫጭር ልብ ወለዶች እንደፃፈ ይነገርለታል፡፡
“ራሴን አጠፋሁ” በ157 ገፆች  ተዘጋጅቶ ና 21፣ አጫጭር ልብ ወለዶችን ይዞ ነው ለገበያ ቀረበው :: በጃፋር መጽሐፍት መደብር አከፋፋይነት በ49 ብር ለገበያ ቀርቧል::