Magazine

ባልታሰሩ ክንፎች መዕሃፍ ተመረቀ

ባልታሰሩ ክንፎች መዕሃፍ ተመረቀ

የጋዜጠኛና ደራሲ ተሾመ ገብረሥላሴ የተዓፈው መጽሐፍ ሜጋቢት 28 ረቡዕ ከቀኑ በዋቢሸበሌ ሆቴል ተመርቆዋል መዕሃፉ ወጎችን፤ ተረኮችን ፤የታሪክ ማስታወሻዎችን፣ ዝርው ግጥሞችንና አጭር ልብወለዶችን ያካተተ ነው ተብላል፡፡

“ጋዜጠኝነትን ሙያዬ ብዬ የጀመርኩት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው”

ያለው ተሾመ፤ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሃላም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ በሸገር ሬዲዮና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ፕሮግራሞችና አምዶችን ከአዘጋጅነት እስከ አርታኢነት እንደሰራ ይናገራል፡፡ ደራሲው “የባህር ጠብታ” የተሰኘውን የመጀመሪያ መጽሐፉን ከ10 ዓመት በፊት ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡ባልታሰሩ ክንፎች መዕሃፍ በ184 ገፆች የተዘጋጀ ሲሆን በ60 ብር ለገበያ እንደቀረበ ለመረዳት ችለናል፡፡