Magazine

“ቃልና ምስል” የተሰኘ የሥዕል ትርኢት በጋለሪያ ቶሞካ ተከፈተ!

“ቃልና ምስል” የተሰኘ የሥዕል ትርኢት በጋለሪያ ቶሞካ ተከፈተ!

የሰዓሊ አገኘሁ አዳነ “ቃልና ምስል” የተሰኘ የሥዕል ትርኢት በጋለሪያ ቶሞካ ተከፈተ:: ለሁለት ወር ለተመልካች ክፍት ሆኖም ይቆያል፡፡ በ ጋለሪያ ቶሞካ ሥዕል ማሳያ የቀረበው “ቃልና ምስል”፤ በድብልቅ ቁስ ጥበባት የተሰሩ የኪነ - ህትመትና የቅብ ሥራዎች ያካተተ ነው፡፡ ለ ኤግዝቢሽኑ በተዘጋጀው የፅሁፍ ማብራሪያ ላይ ሰዓሊ ጥሩነህ እሸቱ ስለ አርቲስቱ ሲናገር፤ “ለሰዓሊና ገጣሚ አገኘሁ አዳነ ሥነግጥማዊ ቃልና ሥዕላዊ ምስል ‹ነፍስና አካል፤ ቃልና ሥጋ› ናቸው፤ አይለያዩም፤ አይነጣጠሉም” ብሏል ፡፡

ሰዓሊው የስዕል ትርኢት በግሉ ሲያቀርብ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አንዱን በስፔን ማቅረቡ ተተቁሟል፡፡ ሰዓሊ አገኘሁ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም የሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ት/ቤት መምህር ሲሆን፣ “ጨለማ ሲበራ” እና “ለምን?” የተሰኙ የግጥም መጻሕፍት ማሳተሙ ይታወሳል፡